የመጀመሪያ ጉዞዎ፣ ደረጃ በደረጃ
Your first ride, step by step
ቅመምን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊጠቀሙ ነው? ከመተግበሪያው መጫን ጀምሮ እስከ መድረሻዎ ድረስ ያለው ሙሉ መንገድ እነሆ።
Using Kimem for the first time? Here is the whole path, from installing the app to arriving at your destination.
ከጉዞው በፊት
Before the ride
መጀመሪያ መተግበሪያውን ከGoogle Play ያውርዱ። ሲከፍቱት በስልክ ቁጥርዎ ይግቡና በSMS የሚላክልዎትን ኮድ ያስገቡ። ከዚያ መተግበሪያው የት እንዳሉ እንዲያገኝ የቦታ ፈቃድ ይስጡ።
First, install the app from Google Play. When you open it, sign in with your phone number and enter the code that arrives by SMS. Then allow location, so the app can find where you are.
ጉዞ መጠየቅ
Requesting the ride
መድረሻዎን ይምረጡ፤ በመፈለጊያው ይጻፉ ወይም የታወቀ ቦታ ይምረጡ። ከማረጋገጥዎ በፊት የዋጋ ግምቱ ይታያል። ሲያረጋግጡ ጥያቄዎ ይላካል፣ ቅርብ ያለው የቅመም ታክሲ ይመደባል።
Choose your destination: type it in the search, or pick a known place. Before you confirm, you see the fare estimate. When you confirm, your request goes out and a nearby Kimem taxi is assigned.
ሾፌሩ ሲመጣ
While the driver comes
ሾፌሩ ሲነሳ መምጣቱን በካርታው ላይ በቀጥታ ይከታተላሉ። የሾፌሩ ስም፣ ተሽከርካሪውና የታርጋ ቁጥሩ በመተግበሪያው ውስጥ ይታያሉ፤ የሚጠብቁትን መኪና አስቀድመው ያውቃሉ።
Once the driver sets off, you watch the taxi come on the map. The driver's name, vehicle, and plate number are shown in the app, so you know which car to expect.
በጉዞው ላይ
During the ride
ጉዞው ሲጀምር ሜትሩ ርቀቱንና ጊዜውን ይቆጥራል። ከፈለጉ የቀጥታ የጉዞ አገናኝ ከጉዞው ውስጥ ሆነው ለቤተሰብ ማጋራት ይችላሉ፤ መንገዱን አብረው ይከታተላሉ።
Once the ride starts, the meter counts distance and time. If you like, you can share a live trip link with family from inside the ride, and they follow along.
ጉዞው ሲያልቅ
At the end
ሲደርሱ ሜትሩ ያሳየውን ለሾፌሩ በጥሬ ገንዘብ ይክፈሉ። የጉዞው መዝገብ በመተግበሪያው ውስጥ ይቀመጣል፣ ለሾፌሩም ደረጃ መስጠት ይችላሉ።
When you arrive, pay the driver in cash what the meter shows. The trip record stays in the app, and you can rate the driver.
ዝግጁ ነዎት? አፑ በGoogle Play ላይ ነው።
Ready? The app is on Google Play.